11/10/2026
የሀዘን መግለጫ
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኢንጅነሪንግ ትምህርት ክፍል የቀድሞ መምህርና የዩኒቨርሲቲያችን ተባባሪ ሬጅስትራል ኃላፊ ሆነው ያገለገሉት ፣ ከዚያም በኋላ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉት ፕሮፌሰር እንጂነር ዘውዱ አብዲ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የዪኒቨርሲቲያችን ማኔጅመንት እና መላው ማህበረሰብ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል::
የዩኒቨርሲቲያች ለቤተሰቦቻቸዉ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል!
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 01/2019 ዓ.ም