Brandagency /ብራንድ ኤጀንሲ

Brandagency /ብራንድ ኤጀንሲ Brand Overseas Employment Agency, P.L.C. is legally registered Company Found in Addis Ababa Ethiopia

23/11/2025
02/12/2024
08/11/2024

Check out BRAND AGENCY’s video.

✨ይህንን ያውቃሉ?በግል ጥረት ከውጪ ሃገር ስራ አግኝታችሁ ለሥራና ክህሎት ሚኒስትር በማሳወቅ ስትሰማሩ የምታገኙት ጥቅም ምንድን ነው?1- በምትሄዱበት ሃገር መብታቸው፣ ደህንነታችሁ እና ክብራ...
27/06/2024

✨ይህንን ያውቃሉ?

በግል ጥረት ከውጪ ሃገር ስራ አግኝታችሁ ለሥራና ክህሎት ሚኒስትር በማሳወቅ ስትሰማሩ የምታገኙት ጥቅም ምንድን ነው?

1- በምትሄዱበት ሃገር መብታቸው፣ ደህንነታችሁ እና ክብራችሁ ተጠብቆ መሥራት እንድትችሉ በመንግስት ከለላ ታገኛላችሁ።

2- በዘላቂነት ህይወታችሁ እንዲቀየር የሥራ ጊዜያችሁን አጠናቃችሁ ወደ ሃገር ስትመለሱ የተለያዩ ማበረታቻ ድጋፎች ይደረግላችኋል።

3- በምትሄዱበት ሃገር መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግላችሁ ይደረጋል።

4- በተሰማራችሁበት ሃገር አሰሪዎቻችሁ እንደማንኛውም ሰራተኞቻቸው መብታችሁን አክብረው አስፈላጊውን ወይም የሚገባችሁን ጥቅማጥቅም እንዲያሟሉላችሁ ይገደዳሉ።

5- የከፋ ነገር ቢያጋጥማችሁ፣ የህክምና ወጪያችሁ እንዲሸፈን፣ አስፈላጊውን ኢንሹራንስ ክፍያ እንዲከፈል እንዲሁም ወደ ሃገራችሁ መመለስ ብትፈልጉ ያለምንም ወጪ መመለስ እንድትችሉ ይደረጋል።

እነዚህን ጥቅሞች የምታገኙት በሥራና ክህሎት ሚኒስትር እውቅና ወደ ውጪ ሃገራት ሥትሰማሩ ብቻ ነው።

ስለሆነም ደህንነታችሁ፣ መብታችሁ እና ክብራችሁ ተጠብቆ እንዲሁም ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ተከብረውላችሁ እራሳችሁን፣ ቤተሰቦቻችሁን እና ሃገራችሁን መደገፍ ትችላላችሁ።

✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
ድህረ-ገፃችንን ይጎብኙ ይመዝገቡ :https://lmis.gov.et

👍 ፌስቡክ : https://www.facebook.com/profile.php?id=61555705001836

📸 ኢንስትግራም፡ https://www.instagram.com/bequ.elmis/

🎥 ዩቲዩብ ፡: https://www.youtube.com/channel/UCiIzqvMmVHMH9g61rc9nX7Q

በኢትዮጵያ እና በኩዌት መንግስት በኩል ኢትዮጵያዉያን ሰራተኞችን ወደ ኩየት ለመላክ ግንቦት ሰኞ 19 2016 ዓ.ም የተደረሰዉን ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ የዉጭ ሀገር ስራ ስምሪት አገናኝ ...
01/06/2024

በኢትዮጵያ እና በኩዌት መንግስት በኩል ኢትዮጵያዉያን ሰራተኞችን ወደ ኩየት ለመላክ ግንቦት ሰኞ 19 2016 ዓ.ም የተደረሰዉን ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ የዉጭ ሀገር ስራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪ ፌዴሬሽን በጽ/ቤቱ ከኩዌት አቻ ማህበር ጋር የዜጎችን መብት ; ክብር እና ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም በዉጭ ሀገር ስራ ስምሪት የተሰማሩ ኤጀንሲዎችን ጥቅም ባስከበረ መልኩ የሁለትዮሽ ስምምነት አፅድቀዋል::

ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ለሁሉም በዉጭ ሀገር ስራ ለተሰማሩ ኤጀንሲዎች በቅርቡ በተከታታይ የምንለቅ ይሆናል::

ፌዴሬሽኑ

29/05/2024

Brand Agency, On Recruitment, WhatsApp Us if you Need Best Manpower Supplier from Ethiopia
094 400 4400

ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ******(ኢ ፕ ድ) ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ...
28/05/2024

ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ፈርመውታል።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤል ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ስምምነቱ ወደ ኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ሕጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

ክቡር አምባሳደር ፈይሰል አልይ በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያዩ።***በቀጠር የመን እና ኢራን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ፈይሰል...
24/05/2024

ክቡር አምባሳደር ፈይሰል አልይ በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከተመራው ልዑክ ጋር ተወያዩ።
***
በቀጠር የመን እና ኢራን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ፈይሰል አልይ በክቡር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ከተመራው እና በቀጠር ዶሃ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ በነበረው የሰራተኛ ዝውውር ዓለም አቀፍ ትስስር መድረክ ላይ ከተሳተፈው ልዑክ ጋር በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ዙሪያ በዶሃ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲው ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይቱ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ስርዓቱን ለማዘመን እና የዜጎችን የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግባራዊ ባደረገው ስርዓቱን የማሻሻል እና የመረጃ አያያዙ የማዘመን ስራ ላይ የተስተዋሉ ችግሮች እና መፍትሄወቻቸው ላይ ያተኮሩ ገንቢ ሀሳቦች ተነስተዋል።
አዲሱ የኦን ላየን የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ወኪሎች ምዝገባ ተጠናቆ ወደስራ መግባቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚቀርፍ ከመሆኑም ባሻገር የዜጎች በህጋዊ መንገድ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሰፊ እድል የሚሰጥ እና የህገወጥ ደላሎችን እኩይ ተግባር ለመከላከል የሚያስችል መሆኑ በውይይቱ ተንጸባርቋል።
ክቡር አምባሳደር ፈይሰል አልይ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪቱን ለማዘመን የተደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀራረብ መወያየት እና ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት የማጥራት ስራ መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን በማውሳት ኤምባሲው ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመመካከር የተጀመረውን ስራ ከውጤት ለማድረስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል
ክቡር ሚኒስትር ደኤታው በአሰራር ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ምክክር ለማድረግ የሚያስችል የጋራ መድረክ የሚፈጠር መሆኑን ገልጸው በስልጠና እና የብቃት ምዘና አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ አሰራሮች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ገልፀዋል።

28/01/2024
05/10/2023

National Day of Kingdom of Saudi Arabia, In Addis Ababa, Ethiopia. September 2023

Address

Mesqel Flower, Gabon Strt
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 18:00
Tuesday 09:00 - 18:00
Wednesday 09:00 - 18:00
Thursday 09:00 - 18:00
Friday 09:00 - 18:00
Saturday 09:00 - 18:00

Telephone

+251944004400

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Brandagency /ብራንድ ኤጀንሲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Brandagency /ብራንድ ኤጀንሲ:

Share