20/10/2026
ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ ተከፈተ
*******
ዜና፡ አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ11 መ/ቤቶች ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በሽያጭ ለማስወገድ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡
በዚህም መሰረት ጨረታው በትናንትናው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአገልግሎቱ አዳራሽ ተከፍቷል፡፡