28/08/2019
በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጣቸው
**********************
ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሀገር ላይ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ እንደተሰጣቸው የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስርያቤቱ ዛሬ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የመጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት ከሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ግንኙነት መሰረት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሄዱ 30ሺህ ዜጎች ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡
እንደ ዶክተር ኤርጎጌ ገለፃ ከዚህ በፊት በሀገወጥ መንገድ ለሄዱት ዜጎች የተሰጠው ህጋዊ ፈቃድ ቢያስደስታቸውም ከዚህ በኋላ በሀገ ወጥ መንገድ ለሚሄዱ ዜጎች ምንም አይነት ምህረት እንደማይደረግና ሲያዙም ቀጥታ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱ መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ ያመለክታል፡፡