New Ethiopia

New Ethiopia ፈጣን ባሉበት ሆነው መረጃወችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ like እና share ማድረጎን አይርሱ እናመሰግናለን

10/08/2026

#የሲቪል ሰርቪስ የሥራ ልምድ መመዘኛ ፎርም!

1. የሠራተኛው መረጃ

* ሙሉ ስም፦ __________________________
* የሥራ መደብ፦ ________________________
* የሚሠራበት መምሪያ/ቡድን፦ _____________

* የሥራ ደረጃ፦ __________________________
* የቅጥር ቀን፦ __________________________
* የሥራ ልምድ ዘመን፦ ____________________
* የቀድሞ የሥራ መደብ/መደቦች፦ ___________

2. የሥራ ልምድ መመዘኛ መስፈርቶች

1. የሥራ ዘመን

* በተያዘው የሥራ መደብ የቆየበት ዘመን፦ __________
* በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ያለው ልምድ፦ __________
* በተዛማጅ የሥራ ዘርፍ ያለው ልምድ፦ ____________

2. የሥራ ዕውቀት

* የሥራውን ተግባርና ኃላፊነት የመረዳት ደረጃ፦ _____________________________________

* የሙያ ዕውቀት ደረጃ፦ _________________

* የሥራ ሂደትና መመሪያ ዕውቀት፦ __________

3. የሥራ አፈጻጸም

* የተሰጠውን ሥራ በጊዜ ማጠናቀቅ፦ __________
* የሥራ ጥራት፦ ______________________
* የሥራ ውጤታማነት፦ _________________
* የተጠያቂነት ደረጃ፦ _________________

4. የችግር መፍታት ችሎታ

* የሥራ ችግርን መለየት፦ _________________
* ተገቢ መፍትሔ ማቅረብ፦ _______________
* ውሳኔ የመስጠት ችሎታ፦ _______________

5. የሥራ ሥነ-ምግባር

* የሥራ ሰዓት አክብሮት፦ ________________
* ታማኝነት፦ __________________________
* ለሥራ ተጠያቂነት፦ ___________________
* የመንግሥት ንብረትና ሀብት አጠባበቅ፦ __________
* የሥራ ሕግና መመሪያ አክብሮት፦ __________

6. የቡድን ሥራ ችሎታ

* ከሌሎች ሠራተኞች ጋር መተባበር፦ __________
* ሀሳብ መለዋወጥ፦ __________
* በቡድን ውስጥ የሚሰጠውን ሚና በአግባቡ መወጣት፦ __________

7. የሙያ ልማት

* በሥልጠና የተሳተፈበት ደረጃ፦ _____________
* አዳዲስ ዕውቀትና ክህሎት የመማር ችሎታ፦ __________
* የተማረውን በሥራ ላይ መተግበር፦ __________

3. የውጤት መመዘኛ

የመመዘኛ መስፈርት ከፍተኛ ነጥብ የተሰጠ ነጥብ

የሥራ ዘመንና ልምድ 15 ___

የሥራ ዕውቀት 15 ___

የሥራ አፈጻጸም 20 ___

የችግር መፍታት ችሎታ 10 ___

የሥራ ሥነ-ምግባር 15 ___

የቡድን ሥራ ችሎታ 10 ___

የሙያ ልማት 15 ___

ጠቅላላ 100 ____

4. የውጤት ደረጃ

90–100 = እጅግ በጣም ጥሩ

80–89 = በጣም ጥሩ

70–79 = ጥሩ

60–69 = መካከለኛ

ከ60 በታች = ማሻሻያ የሚፈልግ

5. የገምጋሚው አስተያየት

የሠራተኛው የሥራ ልምድ፣ ዕውቀት፣ ክህሎት፣ የሥራ አፈጻጸምና የሥነ-ምግባር ደረጃ ተገምግሞ የተገኘው ውጤት፦

6. የገምጋሚው ማረጋገጫ

የገምጋሚው ስም፦ _______

"ገንዘብ አጥቶ ተዋጥቶለት ነው ከእስር ቤት የወጣው የሚባለው ውሸት ነው መውጣት የነበረብኝ አርብ ነበር አንዳንድ የወረቀት ጉዳዮች እስኪያልቁ አርብ ሰዓቱ ደረሰ ቅዳሜ እና እሁድ እዛው ቆይቼ...
05/08/2026

"ገንዘብ አጥቶ ተዋጥቶለት ነው ከእስር ቤት የወጣው የሚባለው ውሸት ነው መውጣት የነበረብኝ አርብ ነበር አንዳንድ የወረቀት ጉዳዮች እስኪያልቁ አርብ ሰዓቱ ደረሰ ቅዳሜ እና እሁድ እዛው ቆይቼ ሰኞ በ800ሺ ብር ዋስ መውጣት ችያለሁ ለመላው አድናቂዎቼ እና ወዳጆቼ እንዴት ናችሁ?"
መንሱር ጀማል

በሸረሪና ምክንያት በሱዳን ጦር ዘንድ መደናገጥ ተፈጥሯል ተባለ‼​ለስድስት ዓመታት የሕወሃት ዋና ማዘዣ የነበረው የሸረሪና ወታደራዊ ካምፕ በመከላከያ እና በተከዜ ዘብ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ በቁጥ...
02/08/2026

በሸረሪና ምክንያት በሱዳን ጦር ዘንድ መደናገጥ ተፈጥሯል ተባለ‼

​ለስድስት ዓመታት የሕወሃት ዋና ማዘዣ የነበረው የሸረሪና ወታደራዊ ካምፕ በመከላከያ እና በተከዜ ዘብ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

በአየርና በእግረኛ ሰራዊት በተካሄደው በዚህ ውጊያ በሕወሃት ላይ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን፣ የሕወሃት ተጨማሪ ኃይል የማስገባት ሙከራም አለመሳካቱ ታውቋል።

​የደረሰው ጉዳት እና የተያዙ ምርኮኞች፦
​የሰው ኃይል፦
📌 ከ195 በላይ ታጣቂዎች መገደ*ላቸውንና
📌ከ176 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን ይጠቁማሉ።
📌በተጨማሪም 121 ታጣቂዎች እና አንድ የኮሎኔል ማዕረግ ያለው የሻለቃ አዛዥ ተማርከው ወደ ባከር ማሰልጠኛ ተወስደዋል ተብሏል።

📌​የጦር መሳሪያዎች፦ ከ450 በላይ ክላሽንኮቭን ጨምሮ፣ ብሬን፣ ዲሽቃዎች፣ RPG፣ ስናይፐር፣ ሞርተሮች፣ ሮኬቶች እና ከ8 በላይ የሬዲዮ መገናኛዎች መማረካቸው ታውቋል።

📌​ቁሳቁስና ተሽከርካሪዎች፦ በፓትሮል ላይ የተመደቡ ዙ-23፣ ወታደራዊና የሎጂስቲክ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ትራክተሮች የወደሙ ሲሆን፤ ጄኔሬተሮችና ሌሎች ቁሳቁሶች ተማርከዋል።

📌​በሌላ በኩል፣ የሸረሪና ካምፕ መያዝን ተከትሎ በሱዳን ጦር በተያዙ አጎራባች የኢትዮጵያ ይዞታዎች ላይ ውጥረት መንገሱ ተገልጿል።

የስራ ማስታወቂያ job vacancy Share ያድርጉ
24/07/2026

የስራ ማስታወቂያ
job vacancy
Share ያድርጉ

በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወይም በብዛት የትኛውን ምልክት ተጠቅማቿል በ emoji ግለፁ✌️✌️🤙🤙
23/07/2026

በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወይም በብዛት የትኛውን ምልክት ተጠቅማቿል በ emoji ግለፁ
✌️✌️
🤙🤙

የሲም ካርድ (SIM card) እድገት ከትልቅ ፊዚካል ካርድ ወደ ኤሌክትሮኒክ (eSIM) የተቀየረበት የ30 ዓመታት የቴክኖሎጂ ጉዞ ነው።​የሲም ካርድ ዋና ዋና የእድገት ደረጃዎች የሚከተሉት ...
23/07/2026

የሲም ካርድ (SIM card) እድገት ከትልቅ ፊዚካል ካርድ ወደ ኤሌክትሮኒክ (eSIM) የተቀየረበት የ30 ዓመታት የቴክኖሎጂ ጉዞ ነው።

​የሲም ካርድ ዋና ዋና የእድገት ደረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
​Full-size SIM (1991)፦ የመጀመሪያው የሲም ካርድ ሲሆን መጠኑም የክሬዲት ካርድ ያህል (85.6 x 53.9 ሚ.ሜ) ትልቅ ነበር።

​Mini-SIM (1996)

ለብዙ ዓመታት በስፋት ጥቅም ላይ የዋለ እና ሁላችንም የምናውቀው መደበኛ የሲም ካርድ መጠን (25 x 15 ሚ.ሜ) ነው።

​Micro-SIM (2003)

የስማርት ስልኮች መምጣት ጋር ተይዞ ቦታ ለመቆጠብ የተሰራ አነስተኛ ሲም (15 x 12 ሚ.ሜ) ነው።

​Nano-SIM (2012

እስካሁን በስፋት በመጠቀም ላይ የሚገኝ፣ ከፕላስቲኩ ይልቅ የቺፑ አካል ብቻ የቀረበት በጣም ትንሽ (12.3 x 8.8 ሚ.ሜ) ሲም ነው።

​eSIM (2016 - አሁን)

በስልኩ ወይም በዲቫይሱ መገጣጠሚያ (Motherboard) ውስጥ አብሮ የተገነባ የኤሌክትሮኒክስ ቺፕ ሲሆን፣ በአካል የሚገባ ፕላስቲክ ሳያስፈልግ በሶፍትዌር ብቻ የሚሰራ ነው።
ጋር New Ethiopia – ከእነርሱ ከፍተኛ ተሳታፊዎች አንዱ በመሆን ወደ እነርሱ ሳምንታዊ የተሳትፎ ዝርዝር ውስጥ ተካትቻለሁ!

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Liyew Messele Etenesh, Mahammad Husseen, Ayenew Ezezew Awoke, Haftamu Kahsay, Dula Go...
23/07/2026

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Liyew Messele Etenesh, Mahammad Husseen, Ayenew Ezezew Awoke, Haftamu Kahsay, Dula Gomasa, Waaqtolee Xiichaa Yiggazuu, Nigus Zena, Erkyihun Uchi Geka, Addition Amenu, Kinfe Gebreal, Zemed Zeleke, Surafel Girma, Asefa Tesema, Woyna Worada, Tarekegn Erjamo, Tegegn Tesema, Tamirat Tesfaye, Erstu Ertro, Kusse Armate, Alii Sanna Gangla, D Zinabu Wedajo Gebru, Firaol Debele, Mintob Lupo, Kindie Derseh, Demissie Daniel, Fute Fulassa, Haile Yesus Eyasu, Bezabeh Tsegaye, Samuel Sambato, Solomon Gemechu Guta, Endale Erjabo Feyisa, Dereje Worku, Alexis Legesse Alexo, Temesgen Melese, Bitew Fentahun, Mekash Kebede, Ye Enate Lij Kali, Tibekel Yoyoo, Mammee Said Muhmed, Simon Tessema, Abebe Edosa, Ayenew Berhanu, Nurgeba Lalega Kemal, ማርሲላስ እንግዳወርቅ, Nahom Mehader, Tamiru Ahmed Mamo, Mohamed Abaneim, Mignot Sisay Shimba, Oddo Wadessa Wata, Chaltu Abereham

    ከእፅዋትመርዞች የልብ በሽታ መድሃኒት የሆነው ዲጎክሲን፣ የደም ማቅጠኛው ዋርፋሪን፣ የወባው መድሃኒት አርቴሜቴር፣ መርዝ ማርከሻው አትሮፒን፣ እንዲሁም የካንሰር መድሃኒቶች ተገኝተዋል። ...
19/07/2026



ከእፅዋትመርዞች የልብ በሽታ መድሃኒት የሆነው ዲጎክሲን፣ የደም ማቅጠኛው ዋርፋሪን፣ የወባው መድሃኒት አርቴሜቴር፣ መርዝ ማርከሻው አትሮፒን፣ እንዲሁም የካንሰር መድሃኒቶች ተገኝተዋል። የኦፒየም ተክል ጥገኛ ህዋሳትንና ተክል በሎችን ለማጥቃት የፈጠረው መርዝ ለህመም ማስታገሻዎቹ ሞርፊንና ኮዴይን ምንጭ ሆኗል።

የእባብ መርዝ ለማከም የሚያስቸግርን ህመምን(intractable pain) የሚያስታግሰውን ኮብራታይድ አስገኝቷል። በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉት የደም ግፊትና የልብ መድሃኒቶቹ ካፕቶፕሪልና ኢናላፕሪን ከመርዘኛ እባቦች የተገኙ ናቸው። በተጨማሪም ከእባብ መርዞች የደም ማቅጠኛ እንዲሁም Reptilase የተሰኘ የቁስል መጠገኛ ተሰርቷል።

ከእንሽላሊት ዝርያዎች መርዝ የስኳር መድሃኒት ተመርቷል።

#በተጨማሪ፦ የእንቁራሪት፣ የአልቅት፣ የንብ፣ የሸረሪት፣ የጊንጥ፣ የቀንድ አውጣ መርዞች ለተለያዩ ፈውሶች መነሻ ሆነዋል።

ከመርዝ መድሃኒት መስራት፣መጥፎ አጋጣሚን በበጎ መውሰድ ሃኪምነት ነው፤በዚሁ የሃኪም አስተሳሰብ፦የብልት ማጠንከሪያው ቪያግራ፣ፀጉር ማብቀያው ሚኖክሲዲል እንዲሁም የፅንስ ማቋረጫ መድሃኒት ከሌሎች መድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳትነት ወደ ፈውስነት ተለውጠዋል፤ Repurpose ተደርገዋል።

በተክስ(Botox)፦አሁን የተለመደ የፊት መዋቢያ እና የነርቭ ህክምና ነው። ይህ ቦቲሊነም ከተሰኘ ከመርዞች ሁሉ የከፋ ጉዳት ካለው የባክቴሪያ ኬሚካል የሚገኝ መድሃኒት ነው።

#ቫይረሶችም ስራ አላቸው በህክምና ክትባትን ለህዋሳት ለማድረስ በተለይም የዘረመል እርማት ህክምና (gene therapy) ለመስጠት በጥገኞቹ ቫይረሶች ላይ ጥገኛ ነን።

#ሃኪሙ ጥፋትን ለልማት የሚያውለው ነው፦ ከፍተኛ የሆነው የወባ ትኩሳት ጨብጥን ለማከም ይውል ነበር። የኮሶ ትልም ውፍረትን ለመቀነስ አገልግሎት ሰጥቷል፤Maggot therapy ለማዳን የሚያስቸግር ቁስልን የሞቱ ህዋሳቱን በዝንብ ላርቫ በማስበላት የማፅዳት (debridement)ዘዴ ነው። Leech therapy አልቅት ለህክምና የሚውልበት ዘዴ ነው። ከፕላስቲክ ቀዶ ጥገና በዃላ አልቅቶች በአዲስ መልክ በተተከለ ቆዳ ላይ የደም ዝውውርን ለማሻሻል ይሰማራሉ።

የዘር ጭፍጨፋ የተደረገባቸው ካምፖች ለህክምና ምርምር አገልግሎት ውለዋል። ለጦርነት ከዋለው የመርዝ ጋዝ የካንሰር መድሃኒት ተፈጥሯል።

ለምንድን ነው ባልጠፋ መቀመርያ እባብ የተመረጠው ?
ሀሳብ ስጡበት ።

     የእንቁላል ቅርፊት በተለይ በሀገራችን በተለምዶ ወደ ቆሻሻ ወይ ወደ ውጪ ከመወርወርና ከመጣል ውጪ ሌላ ጥቅም የለውም።ግን ዜሬ የእንቁላል ቅርፊት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉትና ከነሱም ለኛ ...
17/07/2026



የእንቁላል ቅርፊት በተለይ በሀገራችን በተለምዶ ወደ ቆሻሻ ወይ ወደ ውጪ ከመወርወርና ከመጣል ውጪ ሌላ ጥቅም የለውም።

ግን ዜሬ የእንቁላል ቅርፊት ብዙ ጥቅሞች እንዳሉትና ከነሱም ለኛ ይጠቅመናል የምንለውን እናያለን።

1)የጓሮ አትክልቶትን ከነ ቀንድአውጣ እና ሌሎች ቅጠል በስተው ከሚያበላሹ ትሎች ለመከላከል:-
የዕንቁላል ቅርፊቱን ሰበር ሰበር አድርገው የጓሮ አትክልት ያለበት አፈርና ቅጠሎች ላይ በተን በተን ጣል ጣል አድርጉበት። እንደ ቀንድ አውጣ የመሳሰሉት ለስላሳ ሰውነት ያላቸው ትሎች ስለሚቆርጣቸው ይሸሹታል።

2) የጓሮ አትክልት አፈርን ልማትነቱን ለመጨመር:-
የእንቁላል ቅርፊቱን ደቀቅ አድርገው የጓሮ አትክልት አፈር ላይ በተን ማድረግ የእንቁላል ቅርፊት በካልሲየም እጅግ የበልፀገ ነገር ስለሆነ የአፈሩን ለምነት ይጨምራል። በዛም ምክንያት የእንቁላል ውርፊት ደቀቅ አድርጎ የአትክልት አፈር ላይ መበተን የትኛውንም አትክልት በተለይ ቲማቲምን እንደሚጠቅምና ቶሎ እንደሚያሳድግ በመረጃ የተረጋገጠ ነው።

3) ለዶሮዎች እንዲመገቡ መስጠት:-
ዶሮዎች በተለይ እንቁላል የሚጥሉ ዶሮዎች ካልሲየም ያስፈልጋቸዋል። ስለዚህ መጀመሪያ የእንቁላል ቅርፊቱን በደንብ በመቀቀልና በማድረቅ ከዛም በማድቀቅ የደቀቀውን ቅርፊት ከሌላ ምግብ ጋር በመደባለቅ ለዶሮዎች መስጠት ይቻላል። ይሄም ለዶሮዎቹ በጣም ጠቃሚ ነው።
እሄንን ዘዴ ለሌሎች የቤት እንስሳትም በመጠቀም አጥንታቸው ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉ ማድረግ ይቻላል።

4) ለሰውነታችን ካልሲየምን ለመመገብ:-
ካልሲየም የሚባለው ንጥረ ነገር ለሰውነታችን በተለይ ለአጥንቶቻችንና ለጥርሶቻችን ጥንካሬና ጤንነት አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር ነው።
የእንቁላል ቅርፊት ድግሞ በካልሲየም እጅግ በጣም የበለፀገ ነው።
ስለዚህ የእንቁላል ቅርፊትን መጀመሪያ ከባክቴሪያ ነፃ ለማድረግ ከአምስት ደቂቃ በላይ በሚንተከተክ ውሃ ውስጥ ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በሚንተከተከው ውሃ ውስጥ እንደገባ አረጋግጦ መቀቀል። ከዛ ከተቻለ በኦቭን አሊያም እንዲሁም በደንብ አድርቆ በደንብ መውቀጥ። የተወቀጠውን በሆነ ዕቃ አድርጎ ማስቀመጥ። እሱን እንደገንፎ፣ ወጥ ወይም አጥሚት አይነት ነገሮች ውስጥ በተን እያደረጉ መጠቀም ለሰውነታችን በተለይም ለአጥንቶቻችንና ለጥርሶቻችን ጥንካሬና ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።

የሪህ በሽታ ምንድነው? What is Gouty Arthritis?~~~   ሪህ በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር በመገጣጠሚያዎች ውስጥ ትንንሽ ክሪስታሎች በመከማቸታቸው...
15/07/2026

የሪህ በሽታ ምንድነው? What is Gouty Arthritis?
~~~
ሪህ በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ (Uric Acid) መጠን ሲጨምር በመገጣጠሚያዎች ውስጥ ትንንሽ ክሪስታሎች በመከማቸታቸው የሚከሰት የመገጣጠሚያ በሽታ ነው።

🔍 ምልክቶቹ
µ. በድንገት የሚጀምር ከባድ የመገጣጠሚያ ህመም
µ. እብጠት፣ መቅላት እና ሙቀት
µ. መገጣጠሚያውን ለመንካት እንኳን የሚያስቸግር ህመም
µ. ብዙ ጊዜ የእግር ትልቁን ጣት ይጀምራል፣ ነገር ግን ጉልበት፣ ቁርጭምጭሚት፣ እጅ ወይም ክርን ላይም ሊከሰት ይችላል።
~~
ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች
• ቀይ ሥጋና አንዳንድ የባህር ምግቦችን በብዛት መመገብ
• አልኮል አዘውትሮ መጠጣት
• ውፍረት
• የኩላሊት ችግር
• የቤተሰብ የሪህ ታሪክ

መከላከል ይቻላል?
💧 በቂ ውሃ ይጠጡ።
© ጤናማና ሚዛናዊ አመጋገብን ይከተሉ።
© መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ።
©ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ።
©ተደጋጋሚ የመገጣጠሚያ ህመም ካለዎት የዩሪክ አሲድ ምርመራ በማድረግ ሐኪም ያማክሩ።

ሪህ በትክክል ካልታከመ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን፣ የመገጣጠሚያ ጉዳትን እና የኩላሊት ችግርን ሊያስከትል ይችላል። በጊዜው ህክምና መጀመር አስፈላጊ ነው።

Adresse

Democratic Republic Of The

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque New Ethiopia publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Raccourcis

Partager