Vacancies in Ethiopia - ክፍት የሥራ ቦታ ኢትዮጵያ

Vacancies in Ethiopia - ክፍት የሥራ ቦታ ኢትዮጵያ Receive new job vacancies every day. To post a job, just inbox us. Post your open positions for FREE! Yes, it is free.

የምትኖሩበትን ከተማ፣የትምህርት ደረጃችሁን ፣የሥራ ልምድ (ካላችሁ) እናመቀጠር የምትፈልጉበትን ሙያ እዚህ Comment ላይ አስቀምጡልን::We need more people in various ci...
03/01/2025

የምትኖሩበትን ከተማ፣
የትምህርት ደረጃችሁን ፣
የሥራ ልምድ (ካላችሁ) እና
መቀጠር የምትፈልጉበትን ሙያ እዚህ Comment ላይ አስቀምጡልን::
We need more people in various cities and fields.

ኢሬቻ  #ፊንፊኔ  #2017እንኳን አደረሳችሁ::
06/10/2024

ኢሬቻ #ፊንፊኔ #2017
እንኳን አደረሳችሁ::

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፕ...
29/08/2024

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

እንዲህ አይባልም!==========የሥራ ቃለመጠይቅ ላይ እንዲህ አይባልምአንደኛ------"አሁን የምሰራበት ቢሮ ያስጠላል። አለቃዬ ነዝናዛ ነው። " አይባልም! ለአዲስ ስራ ቃለመጠይቅ ተጠርታች...
04/10/2023

እንዲህ አይባልም!
==========

የሥራ ቃለመጠይቅ ላይ እንዲህ አይባልም

አንደኛ
------

"አሁን የምሰራበት ቢሮ ያስጠላል። አለቃዬ ነዝናዛ ነው። " አይባልም!

ለአዲስ ስራ ቃለመጠይቅ ተጠርታችሁ አሁን የምትሰሩበትን ወይም በፊት የሰራችሁበትን መስሪያ ቤትና አለቆችን ማብጠልጠል ( ቢገባቸውም እንኳን) ያስገምታችሁዋል።

ፈፅሞ አታድርጉት።

" ስራህን ለምን መልቀቅ ፈለግህ" ስባል 'እቅጩን ብናገር ምን ችግር አለው?' ብላችሁ አትሞኙ።

የቀድሞ መስሪያ ቤቱን እና አለቆቹን በስራ ቃለመጠይቅ ላይ የሚወቅስ ሰው ታማኝነትና ሚስጥር ጠባቂነት እንደጓድሉት እና ያልበሰለ ሰው ተቆጥሮ..
" ይሄ ሰውዬ ብንቀጥረው ነገ እኛንም በአደባባይ ከማስጣት አይቆጠብም" ያሰኛል።

እውነት ሆነም አልሆነም ይህን አታድርጉ።

'መስሪያቤቱን ለምን መልቀቅ ፈለግህ?' ብለው ከጠየቁ ልክ ለልብ ወዳጅ እንደሚደረገው ምስጢርና ብሶት ሁሉ አይዘረገፍም።

ሳይዋሽም፣ እንደዚህ አይነት መዘዘኛ ዝርዝር ውስጥ ሳይገባም፣ " አዲስ ነገር እና የስራ ቦታ ስለምፈልግ ነው" ብሎ በደፈናው ማለፍ ብልህነት ነው።

26/07/2023
The reason. Why I don’t watch premier league 😀
05/03/2023

The reason. Why I don’t watch premier league 😀

በአዲሱ ባስ የተሳፈረ ሰዉ ምስክርነት !****************. 🙈 😄 ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር  ስለተገዛው  አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ...
22/02/2023

በአዲሱ ባስ የተሳፈረ ሰዉ ምስክርነት !
****************. 🙈 😄
ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር። ..
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ። በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።..
በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውኑ ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው። በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።..
ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።..
ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል።..
በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።..
ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል። የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።..
በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ 60 60 ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መኔገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል። Thank you አዴክስ ጭሷ!

ዳጊ ነኝ ከገፈርሳ ወንዝ ማዶ :))

dagmawi

░▒▓█►─═ ዥ ዋ ዥ ዌ  ═─◄█▓▒░ነገሩ ሁሉ ዥዋዥዌ የሕፃናት ጨዋታ ሆነ። ሰው ዓለም በቃኝ ብሎ ከመነኮሰ በኋላ ምንድነው እንደዚህ መሆን? በአንብሮተ ዕድ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብተው ለመጨ...
18/02/2023

░▒▓█►─═ ዥ ዋ ዥ ዌ ═─◄█▓▒░

ነገሩ ሁሉ ዥዋዥዌ የሕፃናት ጨዋታ ሆነ።
ሰው ዓለም በቃኝ ብሎ ከመነኮሰ በኋላ ምንድነው እንደዚህ መሆን?
በአንብሮተ ዕድ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብተው ለመጨረሻው መንፈሳዊ ሥልጣን ለሊቀ ጵጵስና በቅተዋል። ምን ቀረኝ ብለው ነው መከራ የሚያዩት? የእግዚአብሔሩስ ይቅር ቀድሞም አልተፈራም።
እንዲያው ሰው ይታዘበኛል አይባልም?
በእውነቱ በዚህ ዕድሜ፥ በዚህ ማዕርግ ዥዋዥዌ መጫወት ያሳፍራል። እውነት ለኦሮሞ ሕዝብ ታስቦ ነው ? በስሙ ተሹማችሁ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ ምን አደረጋችሁለት?
እንደ ሌሎቹ አባቶች በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም እያስተባበራችሁ ለምን የአብነት ት/ቤቶችን አላስፋፋችሁም?

ደግሞስ የእናንተ ሕዝብ ኦሮሞ ብቻ ነው? ሌላውስ ሕዝባችሁ አይደለም? ሌላው ሕዝብ ዝቅ ብሎ ጫማችሁን አልሳመም?
ከፍ ብሎ መስቀላች ሁን አልተሳለመም?
በእጃችሁ አልቆረበም? አባታችን አላላችሁም?
በቋንቋ መማርን ማንም ባልከለከለበት ለምንድነው የዘር ፖለቲከኞችን ቆሻሻ በቅድስናው ስፍራ የምታራግፉት?
ለመሆኑ እናንተ ከእግዚአብ ሔር ሰላምታ ባለፈ በቋንቋው ሰብካችሁ፥ ቀድሳችሁ ታውቃላችሁ?
በቋንቋው መጻፍና ማንበብስ ትችላላችሁ?
ለመሆኑ ለነቀምት ወለጋ ሕዝብስ ከእንግሊዝኛው አማርኛው አይቀርበውም?

ከተሾማችሁ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሞላችሁ።
ሕዝባችን ለምትሉት ስንት መጻሕፍት አዘጋጃችሁለት?
ስንት መጻሕፍትስ ተረጎማችሁለት?
ከአዲስ አበባና ከሱልልታስ ወጥታችሁ ታውቃላችሁ?
እንዲያው እውነቱን እንነጋገርና እንደ አክራሪ የዘር ፖለቲከኞች የአማርኛ ተናጋሪን ፊቱን አያሳየን፥ ድምፁንም አያሰማን ማለት ከአባት ይጠበቃል?
የሾማችሁንስ ሲኖዶስ እንዴት ትክዱታላችሁ?
እውነት ዓላማችሁ ቋንቋ ከሆነ በቋንቋ የሚሰብኩትን እና የሚቀድሱትን የነ አቡነ ናትናኤልን እና የነ አቡነ ሩፋኤልን መንበረ ጵጵስና ለምን በኃይል እየሰበራችሁ ገባችሁ?
በኦሮምኛ የሚሰብኩትን የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን ለምን አሳፈናችሁ?
እነ ምሕረተ አብ ልጆቻችሁ አይደሉም? ምሕረተ አብ እኮ ከእናንተ በላይ በኦሮምኛ ይሰብካል።
በሻሽመኔስ ለምን በካህናትና በምእመናን ደም ላይ ተረማመዳችሁ? ቢያንስ ቢያንስ በእናንተ ምክንያት ስለ ፈሰሰው ደም እና ስላለፈው ሕይወት ሐዘናችሁን ለምን አልገለጣችሁም?

ከጥንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ከኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የወጡ አያሌ ሊቃውንት አሉ። ሃይማኖታቸውን እንጂ ዘራቸውን ስለማይሰብኩ አይታወቁም። በጎንደር በጎጃም ከሊቅነት ጥግ ደርሰው ወንበር ተክለው፥ ጉባኤ ሲያሰፉ፥ ሊቃውንት ሲያበዙ በዚያው የቀሩ አያሌ ናቸው። ሀገራቸው ስለሆነ በደስታ። ሌሎችም አማርኛ እና ትግርኛ ተናጋሪ ሊቃውንት በመላዋ ኢትዮጵያ በገጠርም በከተማም ተበትነው ከፍ ብለው እግዚአብሔርን ዝቅ ብለው ሕዝቡን አገልግለዋል። ተጋብተው ተዋልደው ተዋህደው ኑረዋል። እናንተም የዚህ ውሁድ ውጤት ናችሁ።

ዋናው መታወቅ ያለበት በክርስትና ሃይማኖት የሰው ሃይማኖቱ እንጂ ሌላ ነገር አይጠየቅም። ሥልጣንም ቢሆን በቋንቋ ተሸፍኖ ሳይሆን፥ ተንከራቶ መማር፥ መቃብር ቤት መተኛት፥ ለምኖ መብላት፥ በዚህ መንገድ ማለፍ ያስፈልጋል። እኔ ለወደፊቱ የምፈራው ”የእኔ ቋንቋ ተናጋሪ ጻድቅና ቅዱስ ካልሆነ አን ቀበልም፤ ”እንዳንል ነው።
ምን ቀረን? ዋዜማው ላይ ነን። ”እመቤታችንስ ብትሆን ኦሮምኛም አማርኛም ትግርኛም ጉራጊኛም ተናጋሪ አይደለችም፥ ክርስቶስስ ቢሆን ከአይሁድ ተወለደ እንጂ ከእኛ አልተወለደም፤”
የሚለውም ሳይመጣ ይቀራል?

ቤተ ክርስቲያን በዚህ በተፈጠረው ነገር አትዋረድም። የምንዋረደው እግዚአብሔር ለምን እና እንዴት እንደ መረጠን የዘነጋን ሰዎች ነን። በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ለዓለምና ለዘ ለዓለም ቀድስት ክብርት እና ልዕልት ናት።

መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

01/02/2023

ታኬ የአራዳ ልጅ

ለማመን የሚከብድ ለምስኪን ኢትዮጵያዊ የማይገባ ኔክስት ሌቭል ዘረፋ የሰማሁት ከኤርሚያስ አመልጋ ቀጥሎ በታኬ እኮ ነው እህእ

የመጀመሪያ ታኬ እንደመጣ ያደረገው የሼኩን መሬት መቀማት ነው። 11 መሬቶች ወደ መሬት ባንክ አስመለስኩ ብሎ ጀግና ጀግና ሲጫወት ሰዉም የአብይ ፍቅር ትኩስ የነበረበት ስለነበር አብሮ ተንጫጫ (የዚ ውጤት በኋላ እመለሳለሁ)

ሁለተኛው ዙር ቅርጠፋ የተማሪዎች ምገባ ና ዩኒፎርም ተባለ። በዚህም ለአራት ድርጅቶች ዩኒፎርም አድቫንስ ሲከፈል አንዱ ድርጅት አድቫንሱን 75 ሚል ሙሉ በሙሉ ተከፋፍለው እጄ ላይ የቀረው 16 ሚል ነውና መስሪያ ስለሌለኝ ዩኒፎርሙን ማስረከብ አልችልም የምታስገድዱኝ ከሆነ የወሰዳችሁበትን አወጣለሁ ብሎ ሽምግልና ተልኮ እንደነበር ስንቶቻችሁ ታስታውሳላችሁ🤔

-

ወዲያው የኮተቤ መንገድን መጨረስ ተብሎ የኮተቤ መንገድ ፀሀይ ከጠለቀበት ተክለብርሀን ላይ ተወስዶ ለድሪባ ደፈርሻ (ግማሹን ጀምሮ ስለነበር ያለጨረታ) ጀባ ቢባልም በአገር ልጅነት ተቀባበለ ግን እንዳሰበው ብሩ አልሆነም

ከዛ የሀገር ቤት ኮንትራክተር በዶላር ለአሁኑ የአሜሪካ ጉዞ እንደማያዋጣ የገባው ታኬ የመስቀል አደባባይን ፕሮጀክት ለቻይኖቹ በ2.5 ቢል እና የቄራን መንገድ በኪሜ 400 ሚል ለ4 ኪሜ 1.6 ቢል ያለጨረታ ከፍሎ አስጀመረ (በኢትዮ ታሪክ ውዱ መንገድ የቦሌ መንገድ ሲሆን እሱም በኪሜ 60 ሚል ነበር የወጣበት)

ይህም ከጫማና ከቺክ ያልዘለለ ብር መልሶ ወደ አንደኛው ደንበኛው ወደ ሚድሮክ ፊቱን መልሶ መሬቶቹን በድርድር ግማሹን በአብነት ግማሹን በሚድሮክ ስም በአብዛኛው እንዲመለስ ሆነ። (የአሁኑ የሼኩና የአብነት ክስ ወሎ ሰፈር ጋር ያለውን ማየት ነው) ይህ በዶላር ጉቦ መቀበል ያስጀመረው የመጀመሪያው የመሬት ኬዝ ሙሉ በታኬ ጊዜ የተሰጡ ትልልቅ ካሬዎች ኒዮርክ ብር የገባባቸው ናቸው። (የሸገር ታይምስን ዶክመንተሪ እዩአቸው)

-

በዚህ የጀመረው የታኬና የአብነት እከክልኝ የወርቁን መሬት እኮ ማስመለስ እችላለሁ በሚል ሚድሮክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ሹም ሽር አስነስቶ አረጋን ወደ ዩኒቲ ታከለን ወደ ማእድን አብነትን ወደ ሸራተን የወሰደ ጉዞ ነበር። (ስለ ሚድሮል ካቢኔ ሹም ሽር የአብነት በሼኩ ንብረቶች ላይ ጠቅላይ መሄድና የጀማል ተሽሎክልኮ አለቃውን ማስወጋት ልብወለድ መፅሀፍ የሚወጣው ከአገር መፈንቅለ መንግስት የማያንስ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ይቀመጥልን)

ከዛማ በአመት 600 ሚል ዶላር የሚልከውን የሚድሮክ ጎልድ ንብረት ከጃዋርና ከድንቁ (የጃዌ ባንክ ሮለር በገንዘቡ ጃዌ በአክቲቪስትነቱ ያንን ማእድን ማዘጋቱ ይታወሳል) አፍ ላይ ታኬ ወደ ሼኩ፣ ሼኩም በዱባይ ወደ ታኬ የመጀመሪያው ትራንሳክሽን ተጀመረ። እንደው ሰው ከከንቲባነት ወደ ማእድን ሲመደብ እንዴት እንዳንል (በሲቪል ተመርቆ የመጀመሪያ ስራ ያገኘ የሚል ሚም አስታውሳለሁ😉) ያኔ በጊዜው አበቤ ከንቲባ ካልሆንኩ ብላ አብይን አስቸገረች ተብሎ አይኑ ከታኬ ላይ ተነሳለት።

-

ይህን የለመደው ታኬም ከዚ በኋላ 38 የማእድን ፈቃዶችን ልክ እንደ መሬቱ በመሰረዝ መልሶ መውሰድ የፈለገ ደጅ እንዲጠና በማረግ ያቺኑ ስልቱን ተጠቅሞ ስራውን ጀመረ። አሁን በቅርብ እንኳን የእንግሊዙን ከፊ ሚኒራል ጨምሮ 55 ፍቃዶችን ሰርዞ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ድራማ ሲሰራ ነበር። በወሩ የተመለሰላቸው አየን እንጂ🙄

ከዛማ ታኬ ደስ ሲለው ቢሮዬ እየታደሰ ነው በሚል ቢሮውን ሸራተን፣ ደስ ሲለው መንግስት ቢሮ ውስጥ ማማስ ኪችንን በማስገባት የጀመረው ላግዠሪ ታኬ የአራዳ ልጅ የሚል ማእረግ አሰጥቶታል(በ30 ብር ሰብሲዳይዝድ ምግብ የሚበላ የማእድን ሚኒስቴር ሰራተኛን እና ኮንዶ የወሰደ የእግር ኳስ ደጋፊ አባቴ ቢለው አይደንቅም)። በመጨረሻም ሚሊኒየም አዘጋጅቶ የነበረው የማእድን ኤግዚቢሽን ላይ ለሱና ለጓደኞቹ ፋሽን ሾ በፖዲየሙ ላይ በቫዮሊን ታጅበው እያዩ ውጪ 15 ኩንታል ሲሚንቶ በቸርነቱ እያደለ ነጫጮቹ ድንኳኖች ለሊት በተሰለፉ ሰዎች ሞልቶ ያየሁ ግዜ ግን ለመጀመሪያ በባለስልጣን ያዘንኩበት አጋጣሚ ነበር።

_

አፍሪካ ኢዝ ኤ ዱምድ ኮንቲኔንት። የተለየ የሚያረግ የሚሆን የለም። ታኬም አጦዘው እንጂ ከሽመልስ ወይም ከራሱ ከአብይ የተለየ አስተሳሰብ የለውም። አልፈርድበትም ግን በሌብነቱ እኮንነዋለሁ። ደሞም ለዚ ህዝብ ይገባዋል። ብርሀኑ ለምን ተማሪ ጣለ ብሎ የሚኮንን፣ የሚሰራለት እና የሚሰራበት ያልገባው ህዝብ እንደ ታኬ አይነት አክተር ባለስልጣን በጣም ዲዘርቭ ያደርጋል።

01/02/2023

(አለማየሁ ገመዳ)

የኢትዮጵያ ሀይማኖቶች፦ የዐቢይ አህመድ ፖለቲካዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መሳሪያዎች

ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ሲመጡ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ቀልብ የገዙበትና፣ አስገራሚ ድጋፍ ከሰበሰቡባቸው መንገዶች አንዱ በሀይማኖት ተቋማት አካባቢ የፈጸሟቸው ድርጊቶች ነበሩ። እንደ ኢትዮጵያ አይነት አማኝ በበዛበት ሀገር ወደ ስልጣን ሲመጡ እምብዛም የማይታወቁ የነበሩት ዐቢይ የሀይማኖት ተቋማትን ድጋፍ ካገኙ የማህበረሰቡን ይሁንታ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ በጊዜ የተረዱ ይመስለኛል። በእምነቴ ላይ መንግስታዊ ጣልቃ ገብነት ተፈጽሞብኛል በማለት ከፍተኛ የሀይማኖት መብት እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየውን የሙስሊሙን ማህበረሰብ፣ ኢህአዲግ ሰብስቦ ያሰራቸውን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከሚባሉትና በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያተረፉ ኡስታዞች ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት ሲሞክሩ ማየታችን ለአብነት ሊጠቀስ የሚችል ነው። አንዳንዶቹ ኡስታዞች ዛሬ ከመንግስት ጋር በቅርበት የሚሰሩ ሆነዋል። በሌላ በኩል ኢህአዴግ ከሀገር ባሰናበታቸው 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራ ሲኖዶስ እና በሀገር ውስጥ በተሾሙት አቡነ ጳውሎስ፣ እሳቸው ሲያርፉ ደግሞ አቡነ ማቲያስ ሆነው የውጭ እና የሀገር ውስጥ ሲኖዶስ በመባል ለሁለት ተከፍላ የቆየቸውን ቤተ ክርስቲያን፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀደም ብሎ የተጀመረን የእርቅ ሂደት፣ መንግስታዊ ድጋፍ በመስጠት በምእመኑ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ፈንጠዝያ እንዲፈጠር አድርገዋል። በወንጌላዊ አማኞች (Protestants) ዘንድ ደግሞ መጀመሪያውኑ የኛው ናቸው የሚለው ስሜት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዙሪያቸው የወንጌላውያን እምነት ተከታዮችን ባልተለመደ መልኩ በዙሪያቸው መሰብሰብ፣ ለእንደነ ዮናታን አክሊሉ አይነት ሰዎች ሽልማት መስጠት እና ወዳጅነት መፍጠር እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል።

ይሄ ሁሉ ከሀይማኖቶች ጋር ጥብቅ ግንኙነት መፍጠር ጠቅላይ ሚንስትሩ ለምን ፈለጉ? ቤተ እምነቶችን ለራሳቸውም ሆነ ለድርጅታቸው ድጋፍ ማካበቻ መሳሪያዎች ከማድረግ የዘለለ፣ ለየትኛውም የእምነት ተቋም የተለየ ክብር እንደሌላቸው ማሳያዎች የሚሆኑ የቅርብ ጊዜ ኩነቶችን እናንሳ። ጠቅላይ ምንስትሩ በመጡበት የኦሮምኛ ተናጋሪ ማህበረሰባቸን ባህል ውስጥ ልዩ ስፍራ የሚሰጣቸውን የከረዩ አባ ገዳዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እምበርክከው እንደረሸኗቸውና "ሸኔ ገደላቸው" ተብሎ እንዲነገር መደረጉን የራሳቸው የኦሮሚያ ብልጽግና ባለስልጣናት ተናግረዋል። በሌላ በኩል በወንጌላዊያን አማኞች ዘንድ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የተሰኘ አንጋፋ ተቋም ቢኖርም፣ በጠቅላይ ሚንስትሩ ገፋፊነት የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሚባል አዲስ ስብስብ እንዲቋቋም ማድረጋቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከዚህ ጽሁፍ ጋር በተያያዘው ምስል ላይ እንደሚታየው የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ ባሳለፍነው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ በሚያስገርም ሁኔታ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ተወዳድረው አሸንፈዋል። በእስልምና በኩል መጅሊሱ ውስጥ የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ፣ ለእምነቱ አባት የቀረበ አስታራቂ የሚመስል "እርስዎ እኔን ይወዱኛል?" አይነት አስገራሚ ጥያቄ የታጀበ ቀጥተኛ የሆነ ጣልቃ ገብነት ማሳየታቸውም የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። በየ ቤተ እምነቱ አፍቃሪ ዐቢይ/ብልጽግና የሆኑ የሀይማኖት መሪዎች እንዲኖሩ ጠቅላይ ምንስትሩ አጥብቀው የሚሰሩ ይመስላል። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በአሁኑ ሰአት ያጋጠማት ከዚህ የተለየ ነው ብዬ አላምንም።

በትግራይ ጦርነት ጊዜ "የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት እየተሰራ ነው" በማለት መንግስትን ክፉኛ የተቹት አቡነ ማቲያስን ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደ ወዳጅ ያዩዋቸዋል ማለት የዋህነት ነው። በሌላ በኩል በቅርቡ የቤተ ክህነት ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት አቡነ አብራሃም ለመንግስት የማያጎበድዱ ሰው መሆናቸውን በተደጋጋሚ በሚሰጧቸው መግለጫዎች መገንዘብ ይቻላል። በእነኚህ ሰዎች የምትመራ ተቋም ነች እንግዲህ በአሁኑ ሰአት existential የሆነ ችግር ውስጥ የምትገኘው። አቡነ ማቲያስ በቅርቡ ለህክምና ከሀገር ሊወጡ ሲሉ "ቅርሳ ቅርስ ይዘው ሊወጡ ነው" የሚሉ ወሬዎችን በማናፈስ ፓትሪያርኩ በወጡበት እንዲቀሩ የታሰበ የሚመስል ስራ ሲሰራ ነበር። ይህ ሳይሆን ቀረና ፓትሪያርኩ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ብዙም ሳይቆይ ሶስት ጳጳሳት ራሳቸውን ለይተው "አዲስ ሲኖዶስ አቋቁመናል፤ ኤጲስ ቆጶሳትም ሾመናል" የሚል አስገራሚ ዜና ከኦሮሚያ አካባቢ ሰማን። አቡነ ማቲያስ ውጭ ሀገር ቀርተው ቢሆን ኖሮ እነዚህ ጳጳሳት አላማቸው ምን እንደነበር ቢያንስ አሁን ግልጽ የሆነ ይመስለኛል። ከአመታት በፊት ቤተ ክርስትያኒቱ ውስጥ የተነሳው በቋንቋችን እንሰበክ የሚል ፍትሃዊ ጥያቄ ቤተ ክርስቲያኒቱ ተቀብላ በርካታ ስራዎች እንደሰራች በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚገኙ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ አባቶች ምስክር ናቸው። በቂ ነው ወይ? በቂ እንዳልሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሷ አልካደችም። ነገር ግን OCN (Oromia Clergy Network) የተባለ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚተላለፍ መንፈሳዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከማቋቋም ግን ደርሳለች።

ታዲያ የቤተ እምነቷ ስርአት በማይፈቅደው ሁኔታ አዲስ ሲኖዶስ ማቋቋም ለምን ተፈለገ? ፈተናዎች ቢኖሩም ለምን ውስጥ ሆኖ ለውጦች እንዲመጡ መግፋት አልተፈለገም? ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያንስ በኦሮሚያ መፈንቅለ ሲኖዶስ ለማድረግ ለምን ተፈለገ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ በእኔ አመለካከት በሌሎቹ የእምነት ተቋማት ካየነው የተለየ አይመስለኝም። በኦሮሚያ በንጹሃን ዜጎች ሞት፣ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA/ሸኔ) ጋር በሚደረጉ ውጊያዎችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መቋጨት ባለመቻሉ ህዝባዊ ብሶት የበዛበት እና ከፍተኛ ድጋፍ ማጣትን እያስተናገደ የሚገኘው የኦሮሚያ ብልጽግና፣ በክልሉ በኦርቶድክስ ቤተክርስትያን ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን እየመለሰ የሚያስመስል እንቅስቃሴዎችን በማድረግ፣ ከዋነኛ የክልሉ የፀጥታ መደፍረስ ችግሮች ትኩረትን የማንሳት፣ እንዲሁም "እውነተኛው የኦሮሞ ብሄርተኛ ድርጅት እኔ ነኝ" የሚል መልእክት ለኦሮሚያ ወጣቶች በማስተላለፍ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው። ይህ ደሞ እየተሳካለት እንደሆነ ማሳያ ከሆኑት መካከል በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖች፣ በተለይ የሌላ እምነት ተከታዮች፣ ለዚህ መንግስታዊ ከለላ ለተሰጠው እንቅስቃሴ ድጋፍ እያሳዩ መሆናቸው ነው። ሲኖዶሱ ያወገዛቸው አባቶች መንግስታዊ ድጋፍ እያገኙ እንደሆነ ማሳያዎቹ ምንድናቸው? ተገንጥለው ለወጡት አባቶቹ በፀጥታ ሀይሎች የሚደረግላቸው ጥበቃ፤ እንደ OBS እና Prime Media ያሉ አፍቃሪ-ብልጽግና ሚዲያዎች ለአፈንጋጮቹ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን እየሰጡ መሆናቸው፤ ከዋናው ሲኖዶስ ጥበቃ መነሳቱ፤ አንዳንድ አባቶች ከሲኖዶስ ቅጥር ግቢ ለመውጣት መስጋታቸው፤ ታፍነው የተወሰዱ አባት መኖራቸው፤ የጅማው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በፖሊስ ተይዘው ቆይተው፣ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ሳያስመርቁ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ማንሳት ይቻላል።

እንደተለመደው በጀርባ ስራቸውን እየሰሩ በፊት ለፊት አስታራቂ መስለው ዛሬ በቴለቪዥን የተከሰቱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ አንድ በጣም እያሻሻሉ የመጡት ነገር ቢኖር ቀጣፊነት ነው። መንግስት አንዱን ወገን ደግፎ፣ አንዱን ወገን እያዋከበ ባለበት ሁኔታ መንግስትን "በሀይማኖት ጣልቃ የማይገባ፣" "መካሪ" ብቻ የሆነ አካል አድርገው ለማስቀመጥ የሄዱበት ርቀት እምብዛም አስገራሚ አይደለም፤ ምክንያቱም ይህንን ፊልም ከዚህ በፊት አይተነዋል። መንግስታቸው ዋናው ሲኖዶስ ለእርሳቸው ስላልተመቸ፣ ነባር ጥያቄዎችን የመለሱ በመምሰል፣ "ብልጽግናዊ ሲኖዶስ" የማቋቋም ስራቸውን ከመቀጠል ወደ ኋላ እንደማይሉ ዛሬ በይፋ ያመኑ ይመስላል። ይባስ ብለው የካቢኔ አባላቶቻቸውን "አንድ ሰው ጣልቃ እንዳይገባ" በማለት ሲያስፈራሩም ተደምጠዋል። ምክራቸው ለራሳቸው እንደማይሰራ በተደጋጋሚ ያየነው ቢሆንም፣ ይህኛው ከሀይማኖት እንዲሁም ከብሄር ጋር የተያያዘ አደገኛ አካሄድ ወደ ደም አፋሳሽ ብጥብጥ እያመራ እንደሆነ ማንኛውም አእምሮውን የሚጠቀም ሰው የሚጠፋው አይመስለኝም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ማንንም የሚሰሙ አለመሆናቸውን በተደጋጋሚ አሳይተውናል። የሀይማኖት አባቶች መንግስትን በተደጋጋሚ ለመማጸን እየሞከሩ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት መባባሱ በአስታራቂነት ስም መንግስቴን ያስቀጥልልኛል የሚል የተደናቆረ ፖሊሲ የሚከተል የሚመስለው የብልጽግና መንግስት መካሪ አጥቷ። ይህ አካሄድ ከቁጥጥር ውጭ ከመውጣቱ በፊት መንግስት ጣልቃ ገብነቱን በጊዜ አንስቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሮቻን በውስጧ እንድትፈታ ነፃነቷ ቢሰጣት የሚሻል ይመስለኛል። እንደ አንድ ወንጌላዊ አማኝ (Protestant) ኢትዮጵያዊ ተስፋ ላደርግ የምችለው ይህን ነው። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነውና ብሂሉ፣ ይህ የሀይማኖት ጉዳይ ነውና መንግስት ሆይ ለራስህም ለሀገርም ስትል ተመከር በማለት ጽሁፌን አገባድዳለሁ።

Address

Addis Ababa
20913/1000

Telephone

0921238951

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Vacancies in Ethiopia - ክፍት የሥራ ቦታ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Vacancies in Ethiopia - ክፍት የሥራ ቦታ ኢትዮጵያ:

Share

Category

Our Story

We collect national and international job opening opportunities in Ethiopia and share it to Ethiopians and those interested to work in Ethiopia both home and abroad. We offer job seekers unprecedented free opportunity to receive and retrieve multiple Job openings and opportunities instantly. We provide career advice and job resources to job seekers. We provide head hunting and targeted recruitment services to employers at all sectors. We also serve as a gateway into the huge world of Ethiopia job market, providing institutions an online service to reach more competent and efficient job seekers’ pool. We use all popular social medias including facebook, LinkedIn, twitter and Google+. We are the leading national online career service provider - bridging the gap between employers and job seekers.