03/06/2026
💻 በቴክኖሎጂ ወገኖቻችንን እንፈልግ!
ትናንት በምሥራቅ አርሲ በአሰኮ ወረዳ የተከሰተውን አሳዛኝ ሁኔታ ተከትሎ፣ የጠፉ ወገኖቻችንን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚያገናኝ ቀላል የቴሌግራም ቦት (Bot) በዲጂታል ባለሙያዎቻችን አዘጋጅተናል።
በአሁኑ ሰዓት በርካታ የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎች በመኖራቸው፣ ይህ መድረክ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ሰብስቦ በፍጥነት ለማገናኘት ይጠቅማል።
የቦቱ ሊንክ፦
እንዴት መጠቀም ይቻላል?
ሊንኩን ተጭነው በመግባት Start የሚለውን ይጫኑ።
ቤተሰብ የሚፈልጉ ከሆነ "ቤተሰብ ፈላጊ ነኝ" የሚለውን ቁልፍ ተጭነው ፎርሙን ይሙሉ Telegram በራስ-ሰር ይመራዎታል።
ስለ ጠፉ ወይም ስላሉ ወገኖች ማንኛውም መረጃ ካለዎት "መረጃ አለኝ" የሚለውን ተጭነው ያጋሩን።
ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ጥሪ፦ በቦቱ የሚመጡ መረጃዎችን በፈቃደኝነት ለመለየት፣ ለማጣራት (Data Verification) እና ለተጨነቁ ቤተሰቦች በስልክ ደውሎ መረጃውን ለማድረስ የምትፈልጉ ተመራቂዎች በውስጥ መስመር አግኙን።
እባክዎ ይህ መልዕክት ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ። እውቀታችን ለወገናችን ድምፅ ይሁን!